የአፄ ቴዎድሮስ ቀኝ እጅ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የጦር ጀነራል የነበረ፡፡ ሀገሩን በታማኝነት በቅንነት ያገለገለ የተሰጠውን የራስነት የስልጣን ማዕረግ በስነ ምግባርና በኢትዮጵዊነት መንፈስ ላሳደገኝ ህዝብ እና ለተወለድኩበት አካባቢ ይሁንልኝ በማለት “ራስ” የሚለውን ማእረግ ለጋይንት በመስጠት “ራስ ጋይንት” እንዲባል አድርጓል
ስለዚህ ፊታውራሪ ገብርየ የሰባዊ ድጋፍ እና ልማት ድርጅት” /FGHSDO/ ለህዝብ ከፊት ቀድሞ በመድረስ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ስራዎችን በመስራት የፊት አውራሪነት ሚና እንዲወጣ እና የድርጅቱ አባላት፣የቦርድ አመራር እና ሠራተኞቹ ከራሳቸው ጥቅም፣ ክብር እና ዝና በላይ ለህዝብ እና ለሀገረ የቆሙ የድርጅቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚተጉ እና ለህዝብ የሚሆን የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ እና የስነልቦናዊ ሥራዎችን ለመስራት የሚያስችል ድርጅት እንዲሆን የተሰጠ ስያሜ ነው።